ስቴብልኮይኖች
ዲጂታል ገንዘብ ለዕለታዊ ጥቅም
ስቴብልኮይኖች የETH ዋጋ ቢቀየር እንኳን፣ ቋሚ እሴትን ተመስርተው የተሰሩ የኢቴርየም ቶከኖች ናቸው።

ለምን ስቴብልኮይኖችን?
ስቴብልኮይኖች ያለተለዋዋጭነት ክሪፕቶ ምንዛሬዎች ናቸው። ከETH ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ብዙ ሃይሎችን ይጋራሉ ነገር ግን ዋጋቸው የተረጋጋ ነው፣ ልክ እንደ ተለመደው ምንዛሬ። ስለዚህ በኢቲሪየም ላይ ሊጠቀሙበት የሚችሉትን የተረጋጋ ገንዘብ ማግኘት ይችላሉ። ስቴብልኮይኖች ዋጋቸው እንዴት ሊረጋጋ ቻለ
ስቴብልኮይኖች ዓለም አቀፋዊ ናቸው፣ እና በበይነመረብ ላይ ሊላኩ ይችላሉ። የኤትሬየም ሒሳብ ከያዙ በኋላ ለመቀበልም ሆነ ለመላክ ቀላል ናቸው።
ስቴብልኮይኖችን የማግኘት ፍላጎት ከፍተኛ ነው፣ ስለዚህ የራስዎን ስቴብልኮይኖች በማበደር ወለድ ማግኘት ይችላሉ። ብድር ከመስጠትዎ በፊት አደጋዎቹን ጥንቅቀው ይወቁ።
ስቴብልኮይኖች ወደ ETH እና ወደ ሌሎች የኢተርየም ቶከኖች መለወጥ ይችላሉ። ብዙ dappዎች በስቴብልኮይኖች ላይ ይመሰረታሉ።
ስቴብልኮይኖች የሚጠበቁት በክሪፕቶግራፊ ነው። ማንም ሰው እርስዎን ወክሎ ግብይቶችን ማካሄድ አይችልም።
በመጥፎ የሚታወቀው የቢትኮይን ፒዛ
እ. ኤ. አ. በ 2010 አንድ ሰው 2 ፒዛዎችን በ 10,000 ቢትኮይን ገዛ። በወቅቱ እነዚህ ዋጋ ~$41 አካባቢ ነበር። ዛሬ ባለው ገበያ ይህ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ነው። በኢቴርየም ታሪክ ውስጥም ብዙ ተመሳሳይ የሚያስቆጩ ግብይቶች አሉ። ስቴብልኮይኖች ይህንን ችግር ይፈታሉ፣ ስለዚህ ፒዛዎን ማጣጣም እና ETHዎንም መያዝ ይችላሉ።
ስቴብልኮይን ያግኙ
በመቶዎች የሚቆጠሩ ስቴብልኮይኖች ይገኛሉ። ለመጀመር የሚያግዙዎት ጥቂቶቹ እነሆ። ለኢቴርየም አዲስ ከሆኑ መጀመሪያ አንዳንድ ምርምር እንዲያደርጉ እንመክራለን።
የአርታዒዎች ምርጫ
እነዚህ ምናልባትም በአሁኑ ጊዜ በጣም የታወቁ የስቴብልኮይን ምሳሌዎች ናቸው እናም dappዎችን ስንጠቀም ጠቃሚ ሆነው የምናገናቸው ሳንቲሞች ናቸው።
Dai
Dai ምናልባትም በጣም ታዋቂው ያልተማከለ ስቴብልኮይን ነው። ዋጋው አንድ ዶላር አካባቢ ሲሆን dapps ውስጥ ሰፊ ተቀባይነት አለው።

USDC
USDC ምናልባትም በጣም ታዋቂው በገንዘብ ኖት የሚደገፍ ስቴብልኮይን ነው። ዋጋው አንድ ዶላር አካባቢ ሲሆን በCircle እና በCoinbase ይደገፋል።

ከፍተኛ የገበያ ካፒታል ያላቸው ስቴብልኮይኖች
የገበያ ካፒታል ማለት ጠቅላላው ያሉት የቶከኖች ብዛት ከአንድ ቶከን ዋጋ ተባዝቷል። ይህ ዝርዝር በየጊዜው ይለዋወጣል እና እዚህ የተዘረዘሩት ፕሮጀክቶች በethereum.org ቡድን የሚደገፉ ላይሆኑ የችላሉ።
ገንዘብ | የገበያ ካፒታል | የዋስትና ማስያዣ ዓይነት | ↗ |
---|---|---|---|
![]() | $98,730,445,435 | የገንዘብ ኖት | Go to Tether(opens in a new tab) |
![]() | $28,870,969,833 | የገንዘብ ኖት | Go to USDC(opens in a new tab) |
![]() | $5,014,800,323 | ክሪፕቶ | Go to Dai(opens in a new tab) |
![]() | $1,289,986,442 | የገንዘብ ኖት | Go to TrueUSD(opens in a new tab) |
![]() | $646,584,148 | ስልተ ቀመራዊ | Go to Frax(opens in a new tab) |
ስቴብልኮይንን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል
ቶክኖችን ለመለወጥ የሚረዱ dapps
ከዚህ በፊት ETH እና ቦርሳ ካሎት፣ እነዚህን dapps በመጠቀም ወደ ስቴብልኮይኖች መቀየር ይችላሉ። ስላልተማከሉ ምንዛሬዎች ተጨማሪ
የሚያስፈልግዎት ነገሮች
ምንዛሬ ወይም ቦርሳ ካለው ሒሳብ ክሪፕቶን በቀጥታ መግዛት ይችላሉ። የተወሰነ ETH ለማግኘት ከዚህ በፊት አስቀድመው ተጠቅመው ይሆናል። በሚኖሩበት ቦታ የትኞቹን አገልግሎቶች መጠቀም እንደሚችሉ ይመልከቱ።
በሚኖሩበት ቦታ ሊጠቀሙባቸው የሚችሉዋቸውን አገልግሎቶች ይመልከቱ
የሚያስፈልግዎት ነገሮች
ስቴብልኮይን ዋጋው የተረጋጋ ስለሆነ ለሥራ እና ለአገልግሎቶች በጣም ጥሩ የክፍያ ዘዴ ነው። ነገር ግን ክፍያ ለመቀበል ቦርሳ ያስፈልግዎታል።
ያገኙትን ስቴብልኮይን ለመቀበል ቦርሳ ያስፈልግዎታል
ስቴብልኮይን ከየት እንደሚገኝ
እነዚህ ለስራዎ በስቴብልኮይን የሚከፍሉ መድረኮች ናቸው።
የሚያስፈልግዎት ነገሮች
ስቴብልኮይኖችን ለመበደር ትክክለኛውን dapp መጠቀም ያስፈልግዎታል። እንዲሁም ቦርሳ እና የተወሰነ ETH ያስፈልግዎታል።
Dappን ለመጠቀም ቦርሳ ያስፈልግዎታል።
ለማስያዣ እንዲሁም የግብይት ክፍያዎችን ለመፈጸም ETH ያስፈልግዎታል
የዋስትና ማስያዣ ክሪፕቶ
በኢተርየም ETHዎን ሳይቀይሩ በቀጥታ ከሌሎች ተጠቃሚዎች መበደር ይችላሉ። ይህ የተሻለ ጥቅም ሊሰጥዎት ይችላል - አንዳንዶች ይህን የሚያደርጉት ብዙ ETH ለመሰብሰብ ሲሉ ነው። በክሪፕቶ ስለሚደገፉ ስቶብልኮይንች ተጨማሪ መረጃ
ነገር ግን የETH ዋጋ ተለዋዋጭ ስለሆነ፣ ከበቂ በላይ መጠን ያለው ክሪፕቶ ማስያዝ ያስፈልግዎታል። ይህ ማለት 100 ስቴብልኮይን ለመበደር ከፈለጉ ቢያንስ 150 ዶላር ዋጋ ያለው ETH ያስፈልጎታል። ይህ ስርዓቱን እና አበዳሪዎችን ከጉዳት ይጠብቃል።
ስቴብልኮይኖችን መበደርያ ቦታዎች
እነዚህ dapps ክሪፕቶን እንደ ማስያዣ በመጠቀም ስቴብልኮይኖችን እንዲበደሩ ያስችሉዎታል። አንዳንዶች የተለያየ ቶከኖችን እንዲሁም ETHን ይቀበላሉ።
ስጋቶች
ETHን እንደ ማስያዣ ከተጠቀሙ እና ዋጋው ከወረደ፣ ያስያዙት ETH የተበደሩትን ስቴብልኮይን አይሸፍንም። ይህ ETHዎን እንዲቀንስ ያደርገዋል እና ቅጣት ሊያጋጥምዎት ይችላል። ስለዚህ ስቴብልኮይን ከተበደሩ የETH ዋጋን መመልከት ያስፈልግዎታል። የቅርብ ጊዜ የETH ዋጋ
በስቴብልኮየኖች ይቆጥቡ
ስቴብልኮይኖች ብዙውን ጊዜ ከአማካይ በላይ የወለድ ተመን አላቸው ምክንያቱም እነሱን ለመበደር ብዙ ፍላጎት አለ። የእርስዎን ስቴብልኮይን ወደ አበዳሪ ገንዳ በማስቀመጥ በቅጽበት ወለድ እንዲያገኙ የሚያስችልዎ dappዎች አሉ። ልክ እንደ ባንክ፣ ለተበዳሪዎች ቶከኖችን ያቀርባሉ ነገርግን በማንኛውም ጊዜ ቶከንዎን እና ወለድዎን ማውጣት ይችላሉ።
ወለድ የሚያገኙ dappዎች
ስቴብልኮይኖን ቁጠባዎን ለጥሩ አላማ ያውሉ እንዲሁም የተወሰነ ወለድ ያግኙ። በክሪፕቶ ውስጥ እንዳለ ሁሉም ነገር፣ የተተነበየው አመታዊ መቶኛ ትርፍ (APY) አሁናዊ አቅርቦት/ፍላጎት ላይ በመመስረት ከእለት ወደ እለት ሊለዋወጥ ይችላል።
እንዴት እንደሚሠሩ: የስቴብልኮይን ዓይነቶች
ሁልጊዜ የራስዎን ጥናት ያድርጉ
Algorithmic stablecoins are experimental technology. You should be aware of the risks before using them.በገንዘብ ኖት የሚደገፉ
Pros
- ከክሪፕቶ ተለዋዋጭነት የተጠበቀ።
- የዋጋ ለውጦች በጣም አናሳ ናቸው።
Consኮንስ
- የተማከለ – የሆነ አካል ቶከኖቹን ማጽደቅ አለበት።
- ኩባንያው በቂ መጠባበቂያ እንዳለው ለማረጋገጥ ኦዲት ያስፈልገዋል።
Example projects
በክሪፕቶ የሚደገፉ
የከበሩ ብረቶች
ስልተ ቀመራዊ
ስለ ስቴብልኮይኖች የበለጠ ይማሩ
ማንቸስተር & ትምህርት
- ሂድto Stablecoins.wtf website(opens in a new tab)Stablecoins.wtfStablecoins.wtf በጣም ታዋቂ ለሆኑ ስቴብልኮይኖች ታሪካዊ የገበያ መረጃ፣ ስታቲስቲክስ እና ትምህርታዊ ይዘት ያለው ዳሽቦርድ ያቀርባል።